የመኖቅልቅል፡ መኖን መቀላቀል ዶሮዎች የመምገብ ዋናው አካል ነው። የተዘጋ ጀው ቅልቅል መኖ አግባብ ያለው ካልሆነ የመኖው ጥራት የወረድ እና የዶሮዎ ቹም ምርታማነት የቀነሰ ይሆናል። መኖ በሰው እንዲሁም ያለሰው እገዛ በማሽን ሊዘጋጅ ይችላል። በዚህ መመሪያ ጥርዝ ከዚህ በኋላ በእጅ የሚዘጋጅ መኖ ቅደ ም ተከተል እናያለን።
•በቅልቅሉ ላይ የተጠቀሱትን እያንዳንዱ ግብዓቶች መሰብሰብ እና ማዘጋጀት
•ለመቀላቀል የምንጠቀምበትን ዕቃ ወይም ግድግዳ ማጽዳት
•እያንዳንዱን ግብዓት በአግባቡ መመዘን
•ለመደባለቅ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
•ግብዓቶቹን በቅደም ተከተል መጨመር
•በጎንዮሽ በመግፋት ማደባለቅ
•የተደባለቀውን መኖ በተዘጋጀ ከረጢት ውስጥ መጨመር
አስተውሎት፡ የተደባለቀ የዶሮ መኖ የቆይታ ዕድሜው ሁለት ወር ነው። ነገር ግን የተዘጋጀው መኖ ርጥበት እና ከመደበኛው የተለየ ነገር ካሳየ ለዶ ሮዎቹ መመገብ አያስፈልግም።