አተካከል


ሀ) ችግኝ ማፍላት፣ዘር ማዘጋጀት(ክፍልፋይ ኩርት)

የነጭ ሽንኩርት ዝርያ መምረጥ

የሀገር ውስጥ ዝርያዎች የአካባቢውን ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የተላመዱ በመሆናቸው የሀገር በቀል ነጭ ሽንኩርት ዝርያዎችን መምረጥ፡፡

የአቋሙን ሁኔታ መፈተሽ

የነጭ ሽንኩርት በሽታዎችና ተህዋስያን የሚቀሰቀሱትና የሚተላለፉት በክፍልፋይ ኩርት ውስጥ ስለሆነ ያለፈውን አመት የአቋም ዕድገት መፈተሽ፡፡

መጠን : ከ5-7ግራም፣ ዘሩ በጣም ትልቅ ከሆነ የሽንኩርት ራስ ልኬቱ ወደ ቅጠል ይቀየራል፣ እና ዋናውን ቅጠል ይቀደዋል፡፡ መስፈርት : 2.1-2.6 ቶን/ሄክታር(55000-75000 ኩርት ራስ)

ዘር ማፅዳት

– ‹ኤፕሮን ስታር› የተባለው ፀረተባይ መድሀኒት    የሲይንጄንታ ምርት ነው፡፡ 5ግራም ‹ኤፕሮን ስታር› በ10 ሚሊ ሊትር ውሃ ይሟሟል፡፡

– የነጭ ሽንኩርትን ዘር ከ5-10 ሊትር  መጠን ያለው ማጠራቀሚያ ውስጥ ከፀረ ተባይ መድሃኒቱ ጋር      በማድረግ ከ1-2 ደቂቃ በጥንቃቄ ማደባለቅ፡፡

ለ)  መደብ እና የውሃ መስመር ቱቦ መስራት

ከመዝራታችን ከ1-2 ሳምንት በፊት፡ በመስኩ ላይ ፍግ እና ቀይ አፈር ማድረግ፣

ከመዝራታችን ከ2-4 ቀናት በፊት፡ ማዳበሪያና ፀረ-ተህዋስያን በመስኩ ላይ መዝራት፣ከዛም መደብ እና ውሃ መስመር ቱቦ መስራት፣

ጠቅላላ የባሳል ማዳበሪያ መጠን (ቶን/ሄክታር)

– ቀይ አፈር : 1~1.5

-ፍግ: 20

-የተዋሃደ ሱፐር ፎስፌት : 0.39

-ፖታሺየም ሰልፌት : 0.14

-ዩሪያ : 0.2

መጠን : ከ120-140ሴሜ(መደብ)፣ ከ30-40ሴሜ(መስመር ቱቦ)

ሐ) ንቅለ ተከላ(ጥቁር ፕላስቲክ ማልበስ)

አፈሩን በጥቁር ፕላስቲክ መሸፈን

−የአፈር ሙቀት መጠንን መካከለኛ ማድረግ፣

−በክረምት ወቅት በቅዝቃዜ የሚመጡ ጉዳቶችን መከላከል፣

−የአረም እድገትን መግታት፣

−የአፈር እርጥበትን መጠበቅ፣

ከተዘራ በኋላ መሬቱ እርጥበት እንዳለው ሳይቀዘቅዝ ጥቁር ፕላስቲኩን መሬቱ ላይ ማልበስ፣

በሚያዝያ ወር አጋማሽ ላይ የአየር ፀባዩ አትክልቱን ሊጎዳው ስለሚችል ጥቁር ፕላስቲኩን ማንሳት ወይም ደግሞ ፕላስቲኩን ከማንሳትም ይልቅ የጥቁር ፕላስቲኩን 3ሴሜ ያህል በአፈር በመሸፈን  የአየር ሙቀትን በመከላከል መጠቀም ይቻላል፡፡

ነጭ ሽንኩርት ስር የሚያወጣውና የሚያቆጠቁጠው በተመሳሳይ ጊዜ  ነው፡፡ ክረምትን ከ20-40ሴሜ በመብቀል ያልፋል፡፡ በነሀሴ መጨረሻ    እስከ መስከረም መጀመሪያ የተዘሩ ዘሮች በጥቅምት መጀመሪያ ይበቅላሉ፡፡ በመስከረም መጨረሻ እስከ ጥቅምት መጀመሪያ የተዘሩ ዘሮች ወዲያውኑ  ይበቅላሉ፡፡ ወይም ተክሉ ከ1-2 ቅጠል ይኖረዋል፡፡

ከባድና ባዶ መሬት ከታረሰ በኋላ

ሂደት 1. ባሳል ማዳበሪያ በእርሻ ሜዳው ላይ ማድረግ

የባሳል ማዳበሪያ ብዛቱ እና ስርጭቱ እንደቦታው ስፋት ይለያያል

ሂደት 2. መሬቱን በማረሻ ወይም በበሬ ማረስ

የባሳል ማዳበሪያን ከአፈር ጋር መደባለቅ

የተክሉን ስር በቀላሉ በጥልቀት እንዲያድግ     አፈሩን ማላላት

አረም እንዳይበቅል መከላከል

ሂደት 3. ትክክለኛ ቅርጽ እንዲኖረው አፈሩን መከመርና የመደቡን ጠርዝ ማስተካከል

መደቡን ከሰራን በኋላ የላይኛውን አፈር መደምደምና ማስተካከል

ሂደት 4. የመስኖ ቧንቧ በመደብ ላይ መዘርጋት

ሂደት 5. በጥቁር ፕላስቲክ መሬቱን መሸፈን

መ) መትከል

የክፍልፋይ ኩርት ራስ ጫፍ ወደ ላይ በማድረግና ሰፊው ስር ያለው ጎን ወደታች በማድረግ መትከል፤ የክፍልፋይ ኩርት ራስ ጫፍ ከተዘቀዘቀ፣ ከተገለበጠ ወይም

  በጎን ሆኖ ከተተከለ የሚበቅለው የነጭ ሽንኩርት ቅርጽ ጤናማ አይሆንም፡፡

መትከያ ጊዜ፡ – መሬቱ ከመቀዝቀዙ ከአንድ ወር በፊት

ክፍተቶች፡ – 20 ሴሜ በመደቦቹ መካከል፣ 10ሴሜ በአትክልቶቹ መካከል

ጥልቀት፡ – ከ5-7ሴሜ

የዘር ብዛት፡ – አንድ

ሠ) አገዳዎችን ማስወገድ

  • የነጭ ሽንኩርት አገዳዎች የሚያድጉት የነጭ ኩርት እያደገ ሲመጣ ነው፡፡   
  •  አገዳዎቹን ካላስወገድናቸው የራሱን እድገት ሊያጨናግፍ ይችላል፣
  • አገዳዎች ወዲያውኑ ማስወገድ አለብን፡፡ ጠዋት በጊዜ እና ወይም ፀሐይ      
  • በምዕራብ ስትጠልቅ ለማስወገድ አመቺ ጊዜ ነው፡፡

ረ) አጠቃላይ አያያዝ

ውሃ ማጠጣት

–  የቡቃያውን ዕድገት መጠን ለመጨመር ዘሩን እንደዘራን ወዲያው ውሃ      ማጠጣት አለብን፣

– ዝናብ ከሚዘንብበት አንድ ቀን በፊት መዝራት ጥሩ ሲሆን፣ አየሩ ሞቃታማና ደረቅ ከሆነ መሬቱን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ውሃ ማጠጣት አለብን፣

-ኩርት ለማደግ ብዙ ውሃ ይፈልጋል፡፡ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ የማደጊያ ወቅት   ሲሆን ለጤናማ ኩርት ዕድገት በቂ ውሃ መስጠት አለብን፣

-በቂ ውሃ ካልሰጠን ተክሉ ለዋግ በሽታ ይጋለጣል፡፡ በተጨማሪም የነጭ ሽንኩርት ምርቱን ለመሰብሰብ ከባድ ይሆናል፡፡ በዚህም አገዳው ማደግ ስለማይችል  የመከማቻ ጥራቱ ዝቅተኛ ይሆናል፡፡

Øአረም መቆጣጠር

– አረምን ካልተቆጣጠርን ለማረስ ብዙ ድካምን ይፈጥራል፣ የሚሰበሰበውን     ምርትም ይቀንሳል፡፡