የጉሎ ዋናው ጥቅሙ የሚገኘው ከዘይቱ ነው፡፡ ዘይቱ ከ40-60 በመቶ የፍሬውን ክብደት ይይዛል፡፡ ይህ ዘይት በውስጡ ከ85-90 በመቶ የራቢኖሊክ አሲድ ስላለው ለኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃነት በእጅጉ ይፈለጋል፡፡ ከጥቅሞቹ መካከል ለቀለምና ቫርኒሽ፣ ለናይለን ሥራ፣ ለጨርቃ ጨርቅ፣ ለፀረ አረምና ተባይ፣ በከፍተኛ ሙቀትና ፍጥነት ለሚሽከረከሩ ሞተሮች ቅባት እና ለቅባትና ሽቶዎች ያገለግላል፡፡ቅጠሉ ለሐር ትል ምግብነት ተፈላጊ ነው፡፡ የሐር ምርት በተለያዩ ክልሎች በተለይም በደቡብ፣ በኦሮሚያና አማራ እየተስፋፋ በመሆኑ፤ ጉሎ ለፍሬው ብቻ ሳይሆን ቅጠሉም ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡