የወይን ተክል ችግኝ የሚዘጋጅው በገረዛ ወቅት ነው፡፡ በሳል፣ በበሽታ ያልተጠቃ እና መጠነኛ ውፍረት ያለው አገዳ መርጦ ከአገዳው የመካከለኛ ክፍል አካባቢ ከ3-4 አንጓ ርዝመት ያላቸውን ቁርጥራጮች አዘጋጅቶ ከአናት ያለውን አንድ እምቡጥ ብቻ ትቶ ሌሎቹን በማውጣት ቀደም ሲል ለስልሶ በተዘጋጀ መደብ (ሪጅ) ላይ ወይንም በኘላስቲክ ከረጢት /2ዐ በ16 ሳ.ሜ/ ውስጥ ተክሎ በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ ውሃ ማጠጣት ነው፡፡ በከረጢት ውስጥ ለመትከል 2 እጅ አፈር 1 እጅ አሸዋ እና 1 እጅ ፍግ አደባልቆ ከረጢቱን መሙላት ያስፈልጋል፡፡ የመስኖ ውሃ ችግር ከሌለ ችግኙ ከ5 እስከ 6 ወር ውስጥ ወደ መስክ ማዛወር ይቻላል፡፡