የተፈጥሮ መዛባትን እንዴት እንቆጣጠራለን


ቅርንጫፍ ማብቀል

-የኩርት መጠን ወደ ቅጠልነት ይቀየርና ዋናዎቹን ቅጠሎች ይቀዳቸዋል፣

-የቅጠሉ እድገት በሂደት ላይ በሚሆንበት ወቅት በሚያዝያ ወር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይከሰታል፣

-ከፍተኛ የአየር ሙቀት፣ ክፍልፋይ ኩርቶቹ ሲለያዩ ያለ ከፍተኛ እርጥበት፣   ሰው ሰራሽ የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ እና የቀን ክፍለ ጊዜ አጭር መሆን   ነጭ ሽንኩርትን አላስፈላጊ ቅጠል(ቅርንጫፍ) እንዲያበቅል ያደርጉታል፣

-በጣም የበዛ ዩሪያ፣ ጊዜ ሳይደርስ መዝራት፣ እና ኩርትን ቶሎ መንቀል ክስተቱ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

የመቆጣጠር ዘዴ

-ከ7ግራም በላይ ክብደት ያለው የነጭ ሽንኩርት ዘር አለመጠቀም፣

-አሸዋማ በሆነ አፈር ላይ አለማረስ፣

-ኩርቶችን የምንተክልበት ትክክለኛ ጊዜ መጠበቅ፣

-ክፍልፋይ ኩርት ከተለያዩ በኋላ የበዛ ዩሪያ፣ ፍግ እና ተጨማሪ  ማዳበሪያዎች አለመጠቀም፡፡

ቅጠል ጫፍ መድረቅ(ቲፕ በርን)

-የተክሉ የመጀመሪያ ዕድገት ደረጃና መጨረሻ ዕድገት ደረጃ ላይ የአየር ሙቀት መጠን ከ25ዲሴ በላይ ሲሆን የተክሉ ዕድገት ጥሩ አይሆንም እናም ቅጠሎቹ ወደ ቢጫነት ይቀየራሉ፣

-በአፈር እርጥበት /ድርቀት ምክንያት በአግባቡ ፖታሺየም ባለመውሰድ ይፈጠራል፣

-በተዛባ የኖራ አወሳሰድ ምክንያት በሚፈጠር ድርቀት የቅጠል ጫፍ ይደርቃል፡፡

የመቆጣጠር ዘዴ

-ስሮች አስፈላጊውን ንጥረ ነገር እንዲወስዱ በደረቃማ ወቅት ውሃ ማጠጣት፣

-ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያ በሄክታር ከ15-25 ቶን በየአመቱ ማድረግ በይበልጥ ደግሞ ፖታሺየምን፣ የአፈሩን አሲዳማነት በኖራ ማስተካከል፡፡