የአጨዳ ወቅት


ኑግ ወደ መድረሻው አካባቢ በጣም ስለሚረግፍ ከሌሎች ሰብሎች በበለጠ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡ ከደረሰ በኋላ በመስክ ላይ ብዙ ጊዜ ከቆየ ዘሩ ረግፎ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም የሰብሉን ትክክለኛ የአጨዳ ወቅት መጠበቅ ከሰብሉ የሚገኘውን ምርት እንዳይቀንስ ይረዳል፡፡ ኑግ 50 በመቶ አበባው ከረገፈ ከሶስት ሣምንት  በኋላ እና የተክሉ የላይኛው ቅጠል ከአረንጓዴነት ወደ ቢጫነት ፣ የታችኛው ቅጠል ደግሞ ወደ ቡናማነት ሲለወጥ ቢታጨድ ለምርትም ሆነ ለዘይት ይዘቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በአጨዳ ወቅት ከግንዱ ዝቅ አድርጎ በማጭድ ይቆረጥና ዘሩ እንዳይረግፍ በጥንቃቄ ተይዞ  ወደ መውቂያው ቦታ  መወሰድ ይኖርበታል፡፡

ውቂያና ክምችት

ኑግ ከመወቃቱ በፊት በአውድማ ላይ የዘር እርጥበቱ 10 በመቶ  እስኪደርስ ድረስ መድረቅ ይኖርበታል፡፡ በአውድማ ላይ በዱላ  ወይም በበሬ መውቃት ይቻላል፤ በትራከተር ወይም በመውቂያ ማሽን ሊወቃም ይችላል፡፡ ኑግ ከተወቃ በኋላ የዘር እርጥበቱ ከ8 በመቶ  በታች ሲሆን ንፀህ፣ ደረቅና ነፋሻ በሆነ ማከማቻ ወይም ጎተራ ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

የተሻሻሉ ዝርያዎች

የኑግን ምርታማነት ለመጨመር በተደረጉ ሙከራዎች እስከአሁን አምስት ዝርያዎች ለተጠቃሚው ተለቀዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ብቻ ከምርት ውጭ ሲሆን አራቱ በምርት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምርት ላይ የሚገኙ የኑግ የዝያዎች ዝርዝርና ባህሪያት በሰንጠረዡ ተመልክቷል፡፡

ሰንጠረዝ 1 በምርት ላይ ያሉ የተሻሻሉ የኑግ ዝርያዎችና የአግሮኖሚ ባህሪያቸው

ዝርÃተስማሚ አካባቢየመድረሻ ቀNምርት (ኪ.ግ/ሄ)የዘይት መጠን (በመቶኛ)
ከፍታ (ዥ)የዝናብ መጠን (ሚ.ሜ)በምርምር ማúበገበሬ ማú
ፎገራ ( FOGERA)     እሴቴ (Esate ) ኩዩ (Kuyu ) ሻምቡ-1 (Shambula-1)1600-2200 2200-2700 2200-2700   2000-2400600-1000 600-1000 600-1000   600-1000147 147 147   145900 890 1087   947397 413 –   56039.6 39.6 38.0   39.3