የዘር ወቅትና አዘራር


በዝናብ ለሚለሙ አካባቢዎች የዝናቡ አመጣጥ የዘር ወቅትን ይወስናል፡፡ ለመስኖ ተጠቃሚዎች ግን በመካከለኛው አዋሽ ጥናት መሠረት ግንቦት አጋማሽ ትክክለኛው የመዝሪያ ወቅት ነው፡፡ ይህ ወቅት በመካከለኛው አዋሽ የሙቀት መጠኑ ከፍተኛ የሚሆንበት ነው፡፡ በተመሳሳይ በሌሎች አካባቢዎችም የአካባቢው የሙቀት መጠን ሲጨምር መዘራት እንዳለበት ያስረዳናል፡፡

ዘር ከመዘራቱ ጥቂት ቀናት በፊት ፍሬው ከገለፈቱ መፈልፈል አለበት፡፡ ተፈልፍሎ ብዙ ጊዜ የቆየ ዘር የመብቀል አቅሙ ይቀንሳል፡፡ የምርምር ውጤቶች በመስመሮች መካከል 6ዐ ሣ.ሜ. በተክሎች መካከል ደግሞ 1ዐ ሣ.ሜ. በመተው ከ5 እስከ 7 ሣ.ሜ. ጥልቀት መዝራት ጠቃሚ መሆኑን ያሣያሉ፡፡

ለአንድ ሄክቆር የሚያስፈልገው የዘር መጠን እንደዝርያው የፍሬ ትልቅነትና ትንሽነት የሚወሰን ሲሆን በአማካይ ከ6ዐ እስከ 1ዐዐ ኪ.ግ. የተፈለፈለ ዘር ያስፈልጋል፡፡ ለትላልቅ ፍሬ ያላቸው ዝርያዎች በርካታ  ኪሎ ዘር ሲያስፈልግ ለባለ ትናንሾቹ ዝርያዎች ደግሞ አነስተኛ ኪሎ ይበቃል፡፡