እንቁላል የመፈልፈል ሁኔታ: የዶሮዎች እንቋላል የመፈልፈል ልምዳቸ ው ዋና የመምረጫ መመዘኛ ተደርጎ ባይወሰድም ለሥጋ ተብለው የሚ ረቡ ዶሮዎችን ለእንቋላል ምርት መጠቀም ከተፈለገ እንቁላል መፈልፈ ል በደንብ አለባቸው። ይህንንም ለማወቅ የክንፋቸው ርዝመት፣ የሰውነ ታቸው ቅርጽ እና ለረጅም ሰዓት መቀመጥ እና አለመቀመጣቸው መታ የት አለበት።
2. ከፍተኛ የሆነ የእድገት ሁኔታ፡ ፈጣን የሆነ እድገት የሚያሳዩ ዶሮዎ ች ተፈላጊ ናቸው። ለመራባት አዝጋሚ የሆነ እድገት የሚያሳዩ እንዲ ሁም ለእርድ የደረሱ ትርፍ አውራ ዶሮውች ካሉ እነሱን ማረድ እና ወጪ መቀነስ ያስፈልጋል።
3. ለመፈልፈል የሚሆኑ እንቁላሎችን መለየት፡ መካከለኛ የሆነ መጠን ያላቸው፣ ቅርፊታቸው ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ (ቅርጹ ያልተበላሸ እንዲሁ ም ስንጥቅ የሌለው) እና ቅርጻቸው ልከኛ የሆነ (ታቹ ሰፊ የሆነ እና የ ላይኛው ጫፍ ሾል ያለ) መሆን አለበት።
4. የተፈለፈሉ ጫጩቶች፡ ጥሩ የሆነ ሰውነት ያላቸው እንዲሁም እግ ራቸው እና አይናቸው ላይ ምንም እክል የሌለባቸው መሆን አለበት። በተጨማሪም መኖ አመጋገባቸው እና ውሃ አጠጣቸውን መከታተል ያ ስፈልጋል።
5. በሽታን መቋቋም፡ በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ጥሩ የሆነ ዶሮዎ ችን መምረጥ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ ብዙ ዶሮ ሞቶ ከሚደርስ ኪሳራ ያድናል።