ፓፓያ ፈጥኖ የሚያድግ፣ ቅርንጫፍ የማያወጣ፣ ክፍትና ጠንካራ ያልሆነ ግንድ ያለውና ቅጠለ ሰፋፊ አነስተኛ የፍሬ ዛፍ ነው፡፡ ፍሬው ትልቅና (ከዐ.25 እስከ 5.ዐ ኪ.ግ ክብደት ያለው) ስጋማ ውስጡ ክፍትና በርካታ ትንንሽ ዘሮች ያለው ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፍሬ መጠን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ትንሹ (3ዐ8 እ፺ስከ 25ዐ ግ)፣ መካከለኛው (44ዐ እስከ 33ዐ ግ)፣ ትልቁ (666 እስከ 5ዐዐ ግ) እና በጣም ትልቁ (666 ግ በላይ) ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ትንሹ ለውጭ ገበያ የሚፈለግ ሲሆን ሌሎቹ ግን ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለፋብሪካ ማቀነባበሪያ ይውላሉ፡፡