የፓፓያ ችግኝ ማዘጋጀት


ዳዩሺየስ ችግኝን ባንድ የተከላ ቦታ አንድ ዘር መትከል ሴቴ ወይም ወንዴ ተክል ለማግኘት ያለው ዕድል ከመቶ ሀምሳ እጅ ነው፡፡ የፓፓያ ችግኝ በፕላስቲክ ከረጢት ሲዘጋጅ ባንድ ቦታ ላይ የሚተከለውን የዘር ቁጥር በመጨመር በዚያ ቦታ  ላይ ተፈላጊውን ፆታ  የማግኘት ዕድሉ ይጨምራል፡፡ በተወሰነ ቦታ  ላይ ከመጠን በላይ ዘር መዝራት ችግኞችን ስለሚያቀጭጭ ለሁለት ፆታዊ ፓፓያ ባንድ ቦታ ከ5 እስከ 6 ዘር መትከሉ በቂ ነው፡፡ የዘሩ ቁጥር በመብቀል  ሀይሉና በሚደረግለት እንክብካቤ ይወሰናል፡፡

ለሶሎ ዝርያዎች ባንድ ቦታ  የሚተከለው ዘር አንድ ብቻ ለሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በመብቀል ችሎታ ማነስና በሌሎች ችግሮች ምክንያት የችግኞች ቁጥር እንዳይቀንስ ከ2 እ፺ስከ 3 ቢተከል ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ፓፓያ ሁሉም ተክል ፍሬ ይሰጣል፡፡ ለተከላ እስከሚደርስ በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ ከ4ዐ እስከ 5ዐ ቀናት ስለማቆይ ከረጢቱ ሰፊና ረዘም ያለ እና በቂ አፈር የሚይዝ ሊሆን ይገባል፡፡

በተጨማሪም የችግኙ ዕድገት እንዳይደናቀፍ የውሃ መብዛትም ሆነ ማነስን የጥላ መብዛትን የንጥረ-ነገር ዕጥረትንና በሽታን በባለሙያ እየተገኙ መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡