ቅርንጫፍ ማብቀል
-የኩርት መጠን ወደ ቅጠልነት ይቀየርና ዋናዎቹን ቅጠሎች ይቀዳቸዋል፣
-የቅጠሉ እድገት በሂደት ላይ በሚሆንበት ወቅት በሚያዝያ ወር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይከሰታል፣
-ከፍተኛ የአየር ሙቀት፣ ክፍልፋይ ኩርቶቹ ሲለያዩ ያለ ከፍተኛ እርጥበት፣ ሰው ሰራሽ የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ እና የቀን ክፍለ ጊዜ አጭር መሆን ነጭ ሽንኩርትን አላስፈላጊ ቅጠል(ቅርንጫፍ) እንዲያበቅል ያደርጉታል፣
-በጣም የበዛ ዩሪያ፣ ጊዜ ሳይደርስ መዝራት፣ እና ኩርትን ቶሎ መንቀል ክስተቱ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡
-ከ7ግራም በላይ ክብደት ያለው የነጭ ሽንኩርት ዘር አለመጠቀም፣
-አሸዋማ በሆነ አፈር ላይ አለማረስ፣
-ኩርቶችን የምንተክልበት ትክክለኛ ጊዜ መጠበቅ፣
-ክፍልፋይ ኩርት ከተለያዩ በኋላ የበዛ ዩሪያ፣ ፍግ እና ተጨማሪ ማዳበሪያዎች አለመጠቀም፡፡
ቅጠል ጫፍ መድረቅ(ቲፕ በርን)
-የተክሉ የመጀመሪያ ዕድገት ደረጃና መጨረሻ ዕድገት ደረጃ ላይ የአየር ሙቀት መጠን ከ25ዲሴ በላይ ሲሆን የተክሉ ዕድገት ጥሩ አይሆንም እናም ቅጠሎቹ ወደ ቢጫነት ይቀየራሉ፣
-በአፈር እርጥበት /ድርቀት ምክንያት በአግባቡ ፖታሺየም ባለመውሰድ ይፈጠራል፣
-በተዛባ የኖራ አወሳሰድ ምክንያት በሚፈጠር ድርቀት የቅጠል ጫፍ ይደርቃል፡፡
የመቆጣጠር ዘዴ
-ስሮች አስፈላጊውን ንጥረ ነገር እንዲወስዱ በደረቃማ ወቅት ውሃ ማጠጣት፣
-ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያ በሄክታር ከ15-25 ቶን በየአመቱ ማድረግ በይበልጥ ደግሞ ፖታሺየምን፣ የአፈሩን አሲዳማነት በኖራ ማስተካከል፡፡