የመሬት ከፍታ
ጎመንዘር ከባህር ወለል በላይ ከ 1700-3200 ሜትር ከፍታ የሚበቅል ቢሆንም፤ ለጥሩ ምርት ከ 2000-2600 ሜትር ከፍታ ያላቸው አካባቢዎች ይመረጣሉ፡፡
የአየር ሙቀት
ከፍተኛው የአየር ሙቀት ከ 6.0-25.0 ዲግሪ ሴንቲ ገሬድ በሚደርስበት አካባቢ መመረት የሚችል ሲሆን፤ ለጎመንዘር በጣም ተስማሚ የሚባለው የአየር ሙቀት ግን በአማካይ ከ14.0-17.5 ዲግሪ ሴንቲ ገሬድ ነው፡፡ ጎመንዘር የቀዝቃዛ አካባቢ ሰብል በመሆኑ ቀዝቃዛ አየር ይፈልጋል፤ በተለይ ተዘርቶ እስከሚያብብ ድረስ፡፡ ፍሬ በሚያፈራበት ወቅት ከፍተኛ ሙቀት የዘይት ምርቱን ይቀንሰዋል፡፡
የዝናብ መጠን
በመካከለኛ ጊዜና ዘግይተው ለሚጎመሩ ዝርያዎች ተዘርቶ እስከሚታጨድ ስርጭቱ የተሰተካከለ ከ500 ሚ.ሜ ያላነሰ ዝናብ ይፈልጋሉ፡፡
የአፈር ዓይነት
በጣም ዋልካ (ውሃ የማይተኛበት) እና አሸዋማ ባልሆነ ማንኛውም የአፈር ዓይነት፣ ለምነቱ ጥሩና ኮምጣጥነቱ (PH ) ከ6.0-7.5 በሚደርስ አፈር ላይ በአጥጋቢ ሁኔታ ይመረታል፡፡