የዘር መጠንና አዘራር

የስንዴ የዘር መጠን በረዥም ጊዜ የምርምር ውጤትና በገበሬዎች ተሞክሮ ተረጋግጦ የተወሰነ ነው፡፡ ስንዴ በባህሪው የዘር መጠኑ ሲያንስና ቡቃያው ሲሳሳ የሳሳበትን ክፍት ቦታ ምርታማ የሆኑ ቅጥያዎች በማውጣት ለመሙላት የሚያስችል ተፈጥሮ አለው፡፡  የተሻለ የስንዴን ምርት ለማግኘት በተወሰነ የመሬት ስፋት የሚዘራው የስንዴ መጠን ወሳኝነት ካላቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ የስንዴን የዘር መጠን በጣም ማሳነስ የዘርን ጥራት ለመጨመር ጥሩ ቢሆንም የሰብሉን አጠቃላይ ምርት ግን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ የዘር መጠን መጠቀምም የዘርን ጥራት ከመጉዳቱም በተጨማሪ አጠቃላይ ምርቱንም ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ ጥራት ያለውን ዘርና የተሻለ የስንዴ ምርት ለማግኘት ተገቢውን የዘር መጠን መጠቀሙ አስፈላጊ ነው፡፡

በብተና አዘራር የዘር መጠን

የዘር መጠንና አዘራር የሃገራችን አነስተኛ አርሶ አደሮች እስከ ዛሬ ድረስ የስንዴን ዘር ለመዝራት የተጠቀሙበት (የሚጠቀሙበት) የእርሻ መሳሪያ ባይኖርም በተግባር ግን የዘር እርሻው በባህላዊ ማረሻ እንደተጠናቀቀ 100 ኪ/ግ በሄ/ር ሂሳብ የዳፕ ማደበሪያ በብተና ከዘሩ በኋላ ከ130-150 ኪ/ግ በሄ/ር ሂሳብ የስንዴ ዘሩንም በብተና ይዘራሉ፡፡ ከዚህ በመቀጠል አንድ የመጨረሻ እርሻ በማከናወን የተዘራውን ማዳበሪያና ዘር አፈር እንዲለብስ ያደርጋሉ፡፡ የዚህን ዓይነቱ የአዘራር ዘዴ የተዘራውን ዘር በተመሳሳይ የአፈር ጥልቀት ስለማይሸፍን አበቃቀሉም ሆነ የሰብል አቋም በአንድ ማሳ ውስጥ የተለያዬ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

በመስመር አዘራርና የዘር መጠን

የዘር መጠን

ስንዴ በመስመር ለመዝራት የሚያስፈልገው የዘር መጠን የዘር ብቅለቱ 90% የሆነ 80 -100 ኪ.ግ. ነው፡፡ ይህም በእያንዳንዱ ሳ.ሜ አንድ ዘር፣ በእያንዳንዱ ሜትር 100 ዘሮች ወይም በአንድ ካሬ ሜትር 300 ዘሮችን እንደመጠቀም ይቆጠራል፡፡

የመስመር አወጣጥ

የስንዴ ማሳን በቀላሉ ለማረም፣ ማዳበሪያ በአግባቡ ያለችግር በጎን ለመጨመር እና ማንኛውንም የግብርና ሥራዎችን ለመተግበር እንዲቻል በመስመር መካከል ያለው ስፊት 30 ሳ.ሜ እንዲሆን ታርሶ ለዘር በተዘጋጀው ማሳ ላይ ከ7-10 ሳ.ሜ ጥልቀት ያለው ቦይ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡

የማዳበርያና ዘር አዘራር

በወጣው ቦይ ውስጥ ሁሉንም የተዘጋጀውን ኤን ፒ ኤስ/ዳፕና አንድ ሦስተኛውን ዩሪያ ማዳበሪያ ከ7-10ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ መጨመርና ከ4-6 ሳ.ሜ አፈር መመለስ፣ በተመለሰው አፈር ላይ እንደሚዘራው ለእያንዳንዱ መስመር የሚያስፈልግ ዘር መጥኖ ማዘጋጀት፣ ለመስመር ተመጥኖ የተዘጋጀውን ዘር በሁለት ዘሮች መካከል የሚኖረውን የ 1 ሳ.ሜ ርቀት ጠብቆ በማንጠባጠብ መዝራት፣  የፈሰሰውን ዘር እንደ አፈሩ ዓይነት እና የርጥበት ሁኔታ ከ2 – 4 ሳ.ሜ አፈር ማልበስ፣

የስንዴ ዘር የመዝርያ ጥልቀት

የስንዴ ዘር የመዝሪያ ጥልቀት በአማካኝ ከ3-5 ሳ.ሜ መሆን ያለበት ሲሆን ከዚህ በላይ ዘሩ በአፈር ከተቀበረ የመብቀል አቅሙን ስለሚቀንሰው የሰብሉን አጠቃላይ አቋም ያልተስተካከለ ሲያደርገው ከተጠቀሰው በታች በበቂ ሁኔታ አፈር ካልለበሰ ደግሞ የቅጥያ መፈጠርን ከመቀነሱም አልፎ በደካማ የመሰረታዊ ስር ዕድገት ምክንያት በቀላሉ ሊወድቅ ይችላልል፡፡