የስንዴ ተስማሚ ስነ-ምህዳር


የስንዴ ሰብል ከፍታቸው ከ1500-3200 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ በሆኑ አካባቢዎች ይመረታል፡፡ ይሁን እንጅ የበለጠ የሚስማማው ከፍታው ከ1800-2800 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ሆኖ ከ15-25 ዲግሪ ሴልሽየስ አማካይ የሙቀት መጠን ባላቸው አካባቢዎች ነው፡፡ የዝናብ መጠን ከቦታ ቦታ የተለያየ ቢሆንም በአጠቃላይ ከ500-1200 ሚሊ ሜትር ዝናብ ይፈልጋል፡፡ ስንዴ በጥቁር ሸክላማ፣ በቀይና በቡናማ የአፈር አይነቶች ላይ ይመረታል፡፡ በጣም አሽዋማና ውሃ የሚተኛበት ማሣ ግን ለስንዴ ሰብል አይስማማም፡፡ ለስንዴ ሰብል የሚስማማው የአፈር ጣዕም (የአሲዳማነት ወይም ጨዋማነት ደረጃ) ከ5.5 እስከ 7.5 ፒ.ኤች ድረስ ነው፡፡