የማዳበሪያና ኖራ አጠቃቀም


ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ አጠቃቀም

የሰው ሠራሽ ማዳበሪያ መጠን ከቦታ ቦታ እንደየአካባቢው የአፈር ሁኔታና የስንዴ ዝርያዎች የሚለያይ ሲሆን የአካባቢውን ትክክለኛ የማዳበሪያ ፍላጎት አውቆ መጠቀም ይገባል፡፡ አብዛኛው የአገራችን አፈሮች ለሶስት ንጥረ ነገሮች ማለትም ለናይትሮጅን፣ ፎስፎረስና ሰልፈር አጠቃቀም ላይ ሰብሎች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አርሶ አደሮች ሁለት መሠረታዊ ማዳበሪያዎችን ዩሪያና እና ኤንፒኤስ ማሳ ላይ በመጨመር ከዩሪያ ናይትሮጅንን እንዲሁም ከኤን.ፒ.ኤስ ናይትሮጅን፣ ፎስፎረስና ሰልፈር ስለሚገኙ እነዚህን ሦስት ንጥረ-ነገሮች መጠቀም ይችላል፡፡ ነገር ግን ምክረ-ሃሳብ ላልወጣላቸው እንደ አካባቢው ሁኔታና አፈር ለምነት በምርምር በተገኘ መረጃ መሠረት ኤን.ፒ.ኤስ ከ1-1.5 ኩንታል በሄክታር መጠቀም ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ዩሪያ ማዳበሪያን ከ 1-2 ኩንታል በሄክታር መጠቀም ምርትና ምርታማነትን መጨመር ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ የዳቦ ስንዴ አምራች አካባቢዎች አስፈላጊ የዳፕና ዩሪያ ማዳበሪያ መጠን በሠንጠረዡ ይመልከቱ፡፡

ሰንጠረዥ 3 የማዳበሪያ አጠቃቀም

አካባቢየአፈር ዓይነት/የአካባቢ ስምየማዳበሪያ መጠን ./ሄክታር
ዳፕዩሪያ
አርሲመረሬ10050-100
አርሲጥቁር ቡኒ10050
አርሲቀይ አፈር100-15050
አርሲሳጐሬ አፈር100100-125
አርሲሮቤ100125
ምስራቅ ጐጃምአዴት100150
ደቡብ ጐንደርደ/ታቦር100200
ሰሜን ጐንደርወረራ100160
ደቡብ ወሎወረኢሉ100160
ሰንጠረዥ 3 የማዳበሪያ አጠቃቀም

ኤንፒኤስና ዩሪያ በምንጠቀምበት ጊዜ በምክረ-ሃሳቡ መሰረት በሄክታር የሚያስፈልገውን ሁሉንም ኤን.ፒ.ኤስና አንድ ሦስተኛውን ዩሪያ በመደባለቅ በተዘጋጀው የዘር መስመር (ቦይ) ውስጥ ከ7-10 ሳ.ሜ ጥልቀት ዘር በሚዘራበት ጊዜ መጨመርና በአፈር መሸፈን ነው፡፡ ቀሪውን ሁለት ሶስተኛ ዩሪያ በቡቃያው በውልደት ጊዜ (ከበቀለ ከ35 እስከ 40 ካሉት ቀናት በኋላ) ከሁለተኛው አረም በኋላ በቂ የአፈር ርጥበት ሲኖረ ከመስመሩ ዕዕዋቱ ጎን ከ3-5 ሳ.ሜ ርቀትና ከ3-5 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ መጨመርና በአፈር መሸፈን ነው፡፡ በኤን.ፒ.ኤስ ፋንታ ዳፕ የምንጠቀም ከሆነ የዳፕ እና ዩሪያ አጠቃቀም አጨማመር ተመሳሳይ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከላይ የተገለፁትን የማዳበሪያ ዓይነት፣ የአጠቃቀም መጠን፣ ዘዴ እና ወቅት ከላይ እንደተገለፀው መጠቀም ቢገባም የግብርና ምርምር ማዕከላት ምክረ-ሃሳብ በሰጡባቸው የስንዴ አብቃይ አካባቢዎች ግን የግብርና ምርምር ማዕከላት ምክረ-ሃሳብን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

የተፈጥሮ ማዳበሪያ አጠቃቀም

የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጠቀም የማዳበሪያ አጠቃቀም ብቃትን ያጎለብታል፣ ንጥረ-ነገርንም ይጨምራል፡፡ እነዚህ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች ለዋናና ቅንጣት ንጥረ-ነገሮች ምንጭ ከመሆናቸው በተጨማሪ የአፈር አወቃቀርን በማሻሻል፣ ውሃ የመያዝ ብቃትን በማጎልበት አዎንታዊ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ፡፡ የኬሚካል ማዳበርያ አርሶ አደሮች በሚያዘጋጁት ኮምፖስት ሊታገዝ ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር የማዳበሪያ መጠንን በተመለከተ እንዳለው የማዳበሪያ መጠን ታይቶ የማዳበሪያ ግብዓትን መቀነስ ያስችላል፡፡