ሳይንሳዊ ስያሜ፡(Allium sativum L.)
በተለምዶ አጠራር፡ጋርሊክ(እንግሊዝኛ)፣ ነጭ ሽንኩርት(አማርኛ)
የተገኘበት ሀገር፡ መካከለኛው እሲያ
ነጭ ሽንኩርት አማሬሊዳሲያ በተባለ ቤተሰብ ውስጥ ያለ ዝርያ ነው፡፡ የተገኘውም
ከመካከለኛው እስያ ነው፡፡
በኮሪያ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ምዕራብ እሲያ፣ ህንድ፣ ደቡብ አውሮፓና በአሜሪካ ይበቅላል፣ ይመረታል፡፡
የሚበላውም ክፍል ከተክሉ ስር በላይ ያለው ራስ(ሽንኩርት) ሲሆን ለማደግም ቀዝቃዛ
ወቅትን ይፈልጋል፡፡
የነጭ ሽንኩርት በሶስት መስፈርቶች ይከፈላል፡ – በአገዳ ገፅታ፣ አገዳ ቅርፅ እና
በአስተዳደግ ሁኔታ፡፡
የነጭ ሽንኩርት አበባ ምንም ዘር ስለሌለው ነጭ ሽንኩርት ወይም ኩርትን በአፈር
ውስጥ በመትከል ይራባል፡፡